Alehu Drama Part 7
Description
******************welcome to Kiba Tube************************
This Video all about Channel Opening and tell the community The original Youtube Channel of Kiba Multimedia Production .....
አለሁ! የተሰኘ በአይነቱ እና በይዘቱ ለየት ያለ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ በፋና ቴሌቪዥን ከመጪው አርብ መስከረም 23/2012ዓ.ም ጀምሮ መተላለፍ ይጀምራል፡፡
አለሁ! … በየሳምንቱ አርብ ምሽት የሚቀርብ ሲሆን የእያንዳንዱ ክፍልየድራማ ቆይታ 15 ደቂቃ አለው፡፡ ትኩረቱን በሀገራችን የጤና ስርዓት እና ባለሙያዎች እና በጤና ተገልጋዮች መካከል ያለ ርህራሄ አክብሮት እና እንክብካቤ የተሞላበት የጤና አገልግሎት ላይ ያተኩራል፡፡
ድራማው በፌደራል ጤና ሚኒስቴር ድጋፍ፤ በኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች አስተባባሪነት እና በስድስት የህክምና የሙያ ማህበራት አዘጋጅነት የሚቀርብላችሁ ነው፡፡
ድራማውን በፕሮዲውሰርነት ኪባ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የሚያቀርብ ሲሆን በአማድ ፊልም ደግሞ ቀረፃው ተከናውኗል፡፡ የአለሁ ድራማ ደራሱ እና ዳይሬክተር በዚሁ በፋና ቴሌቪዥን ላይ በሚቀርበው ስራዋ የምታውቋት ደራሲና ዳይሬክተር መዓዛ ወርቁ ናት፡፡
መዓዛ ወርቁ በሀገር አቀፍ እና በኢንተርናሽናል ደረጃ ከተለመደው ወጣ ያሉ የኪነጥበብ ስራዎችን በመድረስ እና በማዘጋጀት ትታወቃለች፡፡ በፋና ቴሌቪዥን የሚቀርበውና አሁን በምእራፍ እረፍት ላይ በሚገኘው ደርሶ መልስ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ደራሲ እና ዳይሬክተር ናት፡፡
አለሁ ድራማ ላይ በርካታ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን መሰረት ህይወት፤ አንተነህ ጌታቸው፣ ፍሬህይወት አረጋ እና ሌሎችም ተሳትፈውበታል፡፡
አለሁ ድራማ ከፊታችን መስከረም 23/2012ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር አርብ ምሽት 3፡30 ላይ ይቀርብላችኋል፡፡ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡
Derso Mels/ደርሶ መልስ
Unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited
Copyright ©2019 ኪባ Kiba Tube
Comments